Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሸዋ ዞን በምርጫ ክልል ደረጃ አሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲዎችን ለመለየት የመራጮች ድምፅ የመሰብሰብ ሂደት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫ ክልል ደረጃ አሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲዎችን ለመለየትየመራጮች ድምፅ የመሰብሰብ ሂደት እየተከናወነ ነው ሲል የምስራቅ ሸዋ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ደበሌ ወርቁ፥ ምርጫው ድምፅ በተሰጠባቸው ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለእንከን ስራዎች በመገባደድ ላይ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ መራጮች በበኩላቸው፥ የምርጫው ሂደት ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንደነበር ተናግረዋል።

ለሀገራቸው ያላቸው ተስፋና የምርጫው ሂደት ፍትሃዊነት ድምፃቸውን በነቂስ ወጥተው ለመስጠት ምክንያት እንደሆናቸው ነዋሪዎቹ አንስተዋል።

በምርጫው የሚያሸንፈውም ሆነ የሚሸነፈው ፓርቲ ሀላፊነት አለባቸው ያሉት ነዋሪዎቹ፥ የሚያሸንፈው የህዝቡን አደራ በመቀበል ለሀገር እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የሚሸነፉ ፓርቲዎችም ይህ የመጨረሻው ምርጫ አለመሆኑን አውቀው በሰላማዊ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ፥ የህዝብን ድምፅ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.