Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ፥ ምርጫውን ለማደናቀፍ ከውስጥም ከውጭም የተደረጉ ሙከራዎች ቢኖሩም ህዝቡ ለነሱ ጆሮ ሳይሰጥ ምርጫው በስኬት ተጠናቋል ብለዋል፡፡

‘‘ምርጫ የዴሞክራሲ መሰረት ነው’’፥ ለዚህ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከጠዋቱ 11ሰዓት እሰከ ምሽቱ 3 ሰዓት ጸሃይ እና ዝናብ ሳይበግራቸው ድምጻቸውን ለሰጡ የክልሉ ህዝብ እንዲሁም ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምርጫው ከለውጡ በኋላ የተደረገ መሆኑ ለየት ያደርገዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ ምርጫው 6ኛ ይባል እንጂ ህዝቡ በዚህ መልኩ አሻራውን ያሳረፈበት እና የዴሞክራሲ ስርዓት የገነባበት የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ ወደአልተገባ አቅጣጫ እንዲሄድ ከሃገር ውስጥም ከውጭም ብዙዎች ቢንቀሳቀሱም ህዝቡ ለሃገር ልማት፣ ለጋራ ዲሞክራሲ የከፈለው ዋጋ ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ሃገር በዚህ መልኩ እንድትገነባ እና የተሻለች ሃገር እንድንገነባ የህይዎት መስዕዋትነት መከፈሉን እና ህይዎታቸውን ማጣታቸውን ኮሚሽነሩ አንስተው፥ ህብረተሰቡም ለሃገር ልማት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.