Fana: At a Speed of Life!

በህዝብ ድምፅ የሚገኘውን ውጤት በጸጋ መቀበል ይገባል- የመዲናዋ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ድምፅ የሚገኘውን ውጤት ማክበር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገራቸው ነዋሪዎች÷ የትናንትናው ድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሰላማዊ ፣ የህዝቡን ጨዋነት እንዲሁም የዓላማ ፅናት ያመላከተ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ፀሀይ፣ ዝናብ እና ብርድ ሳይበግረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በየምርጫ ጣቢያው ተገኝቶ ድምፁን ሲሰጥ የነበረው የመዲናዋ ነዋሪ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዚህ ጨዋነት በተሞላውና ሰላማዊ በሆነ የህዝቡ ተግባርም ኢትዮጵያ ማሸነፍ መቻሏን ነው ነዋሪዎቹ የገለፁት።

ቀጣይነቱ የተረጋገጠ የሀገርን ሰላም ለመጠበቅም አሸናፊ የሚሆነውን የህዝብ ድምፅ በማክበርና በማስከበር ህዝቡ በጀመረው አግባብ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.