Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የተካሄደው ምርጫ በሰላም ተጠናቋል – የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መገራ ምርጫውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ ከምርጫው አስቀድሞ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ኮማንድ ፖስት በመመስረት በቅድመ ምርጫ ፣በምርጫው ዕለትና ከምርጫ በኋላ ሰላም የሰፈነበት ነው ብለዋል።

ለዚህም የሚያስፈልጉ ስራዎችን ለመስራት በታቀደው እቅድና የምርጫ ህጉ በሚያዘው መሠረት ፖሊስ ፍፁም ገለልተኛ በመሆንና ህዝባዊ ወገንተኛነቱን በተግባር በማሳየት ምርጫው መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ትናንት በሁሉም የድሬዳዋ የምርጫ ጣቢያዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩንና ዛሬም የድምፅ ቆጠራ ከተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ምርጫ ክልል ማዕከል እየደረሱ ነው ብለዋል።

የድሬዳዋ ህዝብ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ተባባሪ በመሆን ምርጫው ያለ ፀጥታ ችግር እንዲከናወን ላበረከተው አስተዋፅኦም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአስተዳደሩ ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከመከላከያ እና ከአስተዳደሩ ሚሊሻ ጋር በመሆን በሰራው የተቀናጀ ስራ ምርጫው በሠላም ተካሂዶ በዛሬው ዕለት ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው መመለሱን ኮሚሽነር አለሙ አንስተዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.