Fana: At a Speed of Life!

በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያለውን አግባብ ያልሆነ ጫና በመቃወም በአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፊት ለፊት ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫናችሁን አቁሙ፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን አክብሩ፣ እውነትን እንጂ የፈጠራ ወሬዎችን አትስሙ፣ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች እንዲሁም በትግራይ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ መነሻ የሆነውን አሸባሪ ቡድን አውግዙ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሰልፉ አስተባባሪ የሆነው ዲፌንድ ኢትዮጵያ ቤልጂየም’ አባላት ለአውሮፓ ኮሚሽን እና ለአውሮፓ ምክር ቤት ያዘጋጁትን እና ኅብረቱ በኢትዮጵያ ላይ እያራመደ ባለው አቋም ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የሚገልጽ ግልጽ ደብዳቤ በሰልፉ ቦታ ለተገኙት በኅብረቱ የዓለም ዓቀፍ ትብብር ቢሮ እና የውጭ ጉዳይ ተወካዮች ማስረከባቸውን አስተባባሪዎቹ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.