በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የድምፅ ቆጠራ ተጠናቆ ለምርጫ ክልሎች እየተረከበ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራውን በማጠናቀቅ ለምርጫ ክልሎች እያስረከቡ ነው።
በክፍለ ከተማው ምርጫ ክልል 24 ከሚገኙት 160 ጣቢያዎች ወደ 60 የሚጠጉት እስካሁን ቆጠራውን አጠናቀው ማስረከባቸውን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ፈንታሁን አበራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ቀሪዎቹም ጣቢያዎች እስከ ምሽት ድረስ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በትእግስት ስለሺ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!