Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ሲካሄድ የነበረው ሀገራዊ የምርጫ ሒደት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሲዳማ ክልል ሲካሄድ የነበረው ሀገራዊ የምርጫ ሒደት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ ከዳር እስከ ዳር ሰላማዊ የድምፅ መስጠት ሒደት እንደነበር ገልፀዋል።

የምርጫ ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ የክልሉ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት የተሰጣቸውን ሀላፊነት በመወጣት ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል ።

ህዝቡ በድምፅ መስጠት ሒደቱ ያሳዩት ቁርጠኝነትም የሚደነቅ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ሃላፊው የምርጫው ሒደት ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቅ ይችል ዘንድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የፀጥታ አካላትና የምርጫ አስፈፃሚዎች እንዲሁም መላውን ህዝብ አመስግነዋል።

መራጩ ህዝብም ከነገ ጀምሮ በችግኝ ተከላ ላይ  በመሳተፍ እንዲሁም ሰላም በማስጠበቅ ተግባር ላይ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የድምፅ መስጫ ወረቀት ትላንት የገጠመ ቢሆንም የጎደለውን በመተካትና በሄሊኮብተሮች በማዳረስ ድምፅ እንዲሰጥ መደረግ መቻሉን ገልፀዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.