የመጀመሪያው አለም አቀፍ የሃገር ውስጥ መድኃኒቶች ምርት መድረክ በይፋ ተከፈተ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው አለም አቀፍ የሃገር ውስጥ መደኃኒቶች ምርት መድረክ በይፋ መከፈቱን የጤና ሚንስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ÷ የመጀመሪያው አለም አቀፍ የሃገር ውስጥ ምርት መድረክ በይፋ መከፈቱን ገልጸዋል።
ዶክተር ሊያ አያይዘውም በመክፈቻ ስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የህክምና ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ምርት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት እና እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች ላይ መልዕክት ማስተላለፍ በመቻሌ ደስ ብሎኛል ነው ያሉት፡፡
መድረኩ በአለም ጤና ድርጅት የተጀመረ ሲሆን ጥራት ያለው ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆኑ መድኃኒቶች በአገር ውስጥ ምርትን በማጠናከር ላይ ኢትዮጵያ አጋሮችን እና ባለድርሻ አካላትን በአንድ ላይ በማጥናትና በመወያየት ሁሉን አቀፍ የጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት የተዘጋጀ መርሃግብር ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!