Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ጉብኝታቸውን በማጠናቀቅ ወደ ሩሲያ አቀኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የስራ ጉብኝት አካሄደዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በነበራቸው ቆይታ ከተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸው ይታወሳል።

አቶ ደመቀ በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የነበራቸውን የስራ ተልዕኮ በማጠናቀቅ ወደ ሞስኮ አቅንተዋል፡፡

በሩሲያ በሚኖራቸው የየሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ጉብኝቱም ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማስረዳት እና በሃገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ በይፋዊ ገጹ እንዳስነበበው አቶ ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት በሞስኮ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.