Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ሁሉም ወደ ምርጫ ክልል ደርሰዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ምርጫ ክልል መድረሳቸው ተገለፀ።
በዞኑ ጅማ ከተማን ጨምሮ 18 የምርጫ ክልሎች ያሉ ሲሆን በ 1 ሺህ 583 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምፅ መስጠት ሂደት ሲከናወን ነበር።
አሁን ላይ ድምፅ የተሰጠባቸው ሳጥኖች ያለ ምንም እክል ምርጫ ክልል ደርሰው ቆጠራና ርክክብ እየተደረገ መሆኑን የጅማ ዞን ምርጫ አስተባባሪ አቶ ሸሪፍ አባ ገላን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ለምርጫው ስኬት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉትን የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ ፀጥታ አስከባሪዎችን፣ ወጣቶችንና ህዝቡን አስተባባሪው አመስግነዋል።
በሙክታር ጣሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.