Fana: At a Speed of Life!

የቁማ መካከለኛ ደረጃ የመስኖ ኘሮጀክትን ዳግም ለማስጀመር የ47 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የግንባታ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን በዲዛይን ችግር ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የቆየው የቁማ መካከለኛ ደረጃ የመስኖ ኘሮጀክትን ዳግም ለማስጀመር የ47 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የግንባታ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል።

በሀመር ወረዳ የሚገነባው የመስኖ ኘሮጀክቱ ከተያዘለት የግንባታ ጊዜ ከ10 ዓመት በላይ የዘገየ በመሆኑ በአካባቢው ማህበረብ ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል::

የፌዴራል የዲዛይን እና ሱፐርቪዠን ኮርፖሬሽን የመስኖ ኘሮጀክቱ ያሉበትን ችግሮች በጥናት ከለየ በኋላ ነው ግንባታው ዳግም እንዲጀመር የተወሰነው::

የግንባታ ስራውን ከሚያከናውነው ተቋራጭ ጋር የስምምነት ፊርማ ያኖሩት የደቡብ ክልል የአርብቶ አደር እና ልዩ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ ምትኩ ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ÷ኘሮጀክቱ ከበጀት እና ከጊዜ አኳያ ብክነት የታየበት እንደነበር ተናግረዋል::

ሃላፊው የግንባታ ስራውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንዲቻል የሚመለከታቸው አካላት በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ኘሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 500 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን÷ አጠቃላይ የግንባታ ስራው ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለ ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.