የሀገር ውስጥ ዜና

ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ

By Tibebu Kebede

June 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር ሰላማዊ ሆነ መጠናቀቁን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ማህበረሰቡ፣ የጸጥታ ኃይሉ እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርቧል፡፡

የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ክልሎች የማጓጓዝ ስራም ስኬታማ በሆነ መንገድ ሲተገበር መቆየቱን ነው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ የገለጹት፡፡

ከምርጫው ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚያጣራ የምርመራ ቡድን በክልልና በዞን ደረጃ ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል፡፡

ከምርጫ ጋር ተያይዞም 194 ግለሰቦች ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 103 የሚሆኑት ግለሰቦች ጥቃቅን ስህተቶች የፈፀሙ በመሆናቸው ተገቢውን ምክር ተሰጥቷቸው እንዲለቀቁ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

91 የሚሆኑት ደግሞ ምርመራ ተጣርቶባቸው ለህግ መቅረባቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ÷ ለህግ ከቀረቡት ውስጥ 26 የሚሆኑት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!