የሀገር ውስጥ ዜና

ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ለሀገር ዕድገትና ልማት ፋይዳ አለው – ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ

By Meseret Awoke

June 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ለሀገር ዕድገትና ልማት ፋይዳ እንዳለው ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚደንቷ ‘‘ውመን ፖለቲካል ሊደርስ’’ የተባለ ድርጅት ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጋር በመሆን ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ሴቶችን ይበልጥ ወደ አመራር ለማምጣት ያግዛሉ ብለዉ ያሏቸዉን የመፍትሄ ሀሳቦች አንስተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሴቶችን በአመራር ክህሎት ማሰልጠን፣ በመሪነት ቦታ ላይ ያሉ ሴቶች ለሌሎች የምክርና የስልጠና ድጋፍ መስጠት፣ ሴቶች እርስ በራሳቸዉ የመደጋገፍና አብሮ የመስራት ባህልን ማዳበር እንዲሁም እድሉ ከተሰጣቸዉ ሴቶች ሰርተዉ ማሳየት እንደሚችሉ ማመን ይገኙበታል፡፡

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ በኢትዮጵያ ሴቶችን ለአመራር ከማብቃት አኳያ በተለያዩ ደረጃዎች እየተተገበሩ ያሉ መርሀ ግብሮች ማስጀመራቸዉን ጽህፈት ቤቱ አስታውሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!