Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጄምስ ዋኒ ኢጋ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ።
አምባሳደር ነቢል የሁለቱ አገራት የጠነከረ ግንኙነትን በማንሳት የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨባጭ የልማት ሥራዎች መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከዚህ አንጻር ሁለቱን አገራት በመንገድና በኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር የተጀመረው ጥረት እንዲሳካ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በጎረቤት አገራት ጭምር ለማስጀመር የያዘችውን ዕቅድ ለምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በተጨማሪ አምባሳደሩ በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ አስመልከቶ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን 6ኛው አገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያሸነፉበት ነጻና ሰላማዊና ምርጫ ሆኖ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዋኒ ኢጋ የሁለቱን አገራት ግንኑነት የበለጠ ለማጠናከር የመሠረተ-ልማት ትስስሮች ላይ ማተኮር ተገቢ መሆኑን አውስተዋል፡፡
6ኛው አገራዊ ምርጫ በሰላም በመጠናቀም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
እንዲሁም የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለደቡብ ሱዳንና ለአካባቢው ትልቅ ጸጋ መሆኑን፤ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በውይይት ብቻ መፍታት የሚገባው መሆኑን በውይይቱ ወቅት መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.