የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ገመገመ

By Tibebu Kebede

June 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት መገምገሙን አስታወቁ፡፡

ግምገማው በቅድመ ምርጫ ዝግጅት፣ በምርጫ ክንውን፣ በሕዝብ ተሳትፎ እና በአጠቃላይ የምርጫው ሂደት ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ኮሚቴው ከጠቅላላ ሂደቱ ጋር በተያያዘም ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችን መለየቱን ጠቁመዋል፡፡

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሰላም እና ደኅነት እንዲሁም በቀጣይ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!