ኢትዮጵያን እናልብሳት ሀገራዊ ችግኝ ተከላ ማብሰሪያና የአብሮነት መርሃ ግብር በአርሲ ዞን ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን እናልብሳት ሀገራዊ ችግኝ ተከላ ማብሰሪያና የአብሮነት መርሃ ግብር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የተወጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ከሰላማዊው ምርጫ ማግስት መሆኑ ልዩ ስሜት እንዳለው አቶ አባ ዱላ ገመዳ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሁላችንም ህብረት ታምራለች ያሉት በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ወጣቱ ጥላቻና መከፋፋልን በመንቀል ፍቅርና አንድነትን መትከል አለበት ብለዋል፡፡
መሰል የአብሮነት መርሃ ግብር በቀጣይ ጊዜያቶችም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡
በስንታየሁ አበበ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!