Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ስርዓቱን የጠበቀ እና ዜጎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉበት ነበር – ኢሠማኮ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስርዓቱን የጠበቀ እና ዜጎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታውቋል፡፡

የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ÷ በምርጫው ዕለት 1ሺህ 130 ታዛቢዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በ24 የክልል ከተሞች መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

ታዛቢዎቹ በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎችም ዜጎች ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን እና የምርጫ አስፈፃሚዎችም ገለልተኛ እንደነበሩ መታዘባቸውን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ እጥረት ማጋጠሙን እና በተወሰኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ ድግሞ የክህሎት ማነስ መስተዋሉን አመልክተዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱ ከየትኛውም የውጭ ሃይል ተፅዕኖ ነፃ በመሆኑም ማህበረሰቡ በነፃነት የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ መቻሉን አውስተዋል፡፡

በኮንፌዴሬሽኑ የተመደበ አንድ የምርጫ ታዛቢም ያለ አግባብ በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ ከሰዓታት ቆይታ በኋላ መፈታቱን ገልጸዋል፡፡
በመታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.