Fana: At a Speed of Life!

በጥሎ ማለፉ ቤልጂየም ከፖርቹጋል እንዲሁም ጀርመን ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ተፋላሚዎች ተለይተዋል፡፡

የውድድሩ የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ሲጠናቀቁ፥ ፈረንሳይ፣ ፖርቹጋል እና ጀርመን ከተደለደሉበት ምድብ ተያይዘው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ፈረንሳይ ከፖርቹጋል እንዲሁም ጀርመን ከሃንጋሪ በተመሳሳይ ሁለት አቻ ተለያይተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ፈረንሳይ ምድቡን በበላይነት ስታጠናቅቅ ፖርቹጋል እና ጀርመን ተከታይ ሆነው ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ጥሎ ማለፉ ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ዴንማርክ ከዌልስ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡

ምሽት 4 ሰአት ላይ ደግሞ ምድብ አንድን በበላይነት ያጠናቀቀችው ጣሊያን ከኦስትሪያ ትጫወታለች፡፡

በማግስቱ እሁድ ኔዘርላንድስ ከቼክ ሪፐብሊክ ሲጫወቱ ተጠባቂው የቤልጂየም እና ፖርቹጋል ጨዋታም ምሽት 4 ሰአት ይደረጋል፡፡

ሰኞ በሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ደግሞ ክሮሺያ ከስፔን እንዲሁም ፈረንሳይ ከስዊዘርላንድ ይገናኛሉ፡፡

የጥሎ ማለፉ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር እንግሊዝ ከጀርመን እንዲሁም ስዊድንን ከዩክሬን ያገናኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.