ጤና

ዋና ዋና የጉበት ህመም ምልክቶች

By Meseret Awoke

June 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉበት ህመም (ሄፐታይተስ) አምስት ዋና ዋና ምልክቶች አሉት፡፡

ከጉበት ህመም አንዱ ምልከት ተደርጎ የሚወሰደው ድካም ሲሆን፥ የጉልበት ማጣት ፣ ከስራ ወይም ከእንቅስቃሴ በኋላ የሚመጣ ድካም ነው፡፡

ብዙ ጊዜ ምልክቱ ከጠዋት ይልቅ በማታ ያጋጥማል ፣ በጉበት በሽታ ምክንያት የሚመጣ ድካም አልፎ አልፎ የሚመጣና በተለያየ ጊዜ የድካሙ ክብደት የሚለያይ ነው፡፡

የማቅለሽለሽ ስሜት ደግሞ ሌላኛው የህመሙ ምልክት ሲሆን፥ ከፍተኛ የሆነ የጉበት ህመም ላይ የሚከሰት እና ከድካም የህመም ስሜት ጋርም አብሮ ሊኖር የሚችል ነው፡፡

ይህ የህመም ስሜት ሽታ ባላቸው ምግቦች እና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች በመመገብ ይባባሳል፡፡

የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም ደግሞ በብዙ አይነት የጉበት በሽታዎች የሚከሰት ሲሆን፥ የሰውነት ቆዳ ማሳከክ ሌላው ህመሙ ምልክት ነው፡፡

የአይን ነጭ ክፍል እና የቆዳ ቢጫ መሆን እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ አይን አረንጓዴ ሊሆን ሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችል ሲሆን፥ ይህ ከመከሰቱ በፊት የሽንት ቀለም መጥቆር እንደሚያጋጥም ከደቡብ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!