የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የላሙ ወደብን ሊጎበኙ ነው

By Meseret Demissu

June 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከተለያዩ የግልና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የላሙ ወደብን ሊጎበኙ ነው።

በቅርቡ በኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የተመረቀው የላሙ ወደብ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የተጀመረ የጋራ ፕሮጀክት ነው፡፡

ጋዜጠኞቹ  ከሰኔ 17 እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በኬንያ በሚኖራቸው ቆይታ ከላሙ ወደብ  በተጨማሪ ተዛማጅ ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚያም ባለፈ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት በአገራቸው የሚያደርጉትን ተሣትፎ የተመለከተ  ጉብኝት እንደሚያደርጉ ኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!