የሀገር ውስጥ ዜና

የጌዴኦ ዞን የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባውን አካሄደ

By Tibebu Kebede

June 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባውን አካሄደ፡፡

ስብሰባው በምርጫው አጠቃላይ ሂደትና አጋጥመዋል ባሏቸው ችግሮችና ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሰላም መርጦ መግባቱ የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ የሰጠውን ድምፅ ማክበር ደግሞ ከፓርቲዎች እንደሚጠበቅም ነው የተናገሩት፡፡

አያይዘውም የተነሱ ችግሮች በምርጫ ቦርድ ታይተው ምላሽ እስከሚሰጥ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በታሪክነሽ ሴታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!