Fana: At a Speed of Life!

74 ዜጎች ከሊባኖስ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 74 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡
በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ከሚመለከታቸው የሊባኖስ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ሰነድ አልባና የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ዛሬ ከተመለሱት መካከል 16 የሚሆኑ ዜጎች አሜል ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የኮሮና ምርመራና የትኬት ወጫቸውን መሸፈኑን በቤሩት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.