Fana: At a Speed of Life!

ለዘላቂ ሠላምና ልማት አብሮነታችንንና አንድነታችንን እናጠናክራለን- የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በይቅርታ ተሻግረን ለዘላቂ ሠላምና ልማት አብሮነታችንና አንድነታችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ በእርቀ ሰላም ኮንፈረስ ላይ የተገኙ የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
በመተከል ዞን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የዜጎች ሞትና መፈናቀል ለማስቀረት የተቋቋመው የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት በሰራው ስራ÷ አሁን በአካባቢው አንፃራዊ ሠላም በመስፈኑ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አካባቢያቸው ጊዜያዊ ማረፊያ እየተመለሱ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በተካሄደው የእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ ከፍተኛ የመንግስት፣ የመከላከያ የስራ ኃላፊዎች፣ ከ22 ቀበሌ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች እንዲሁም የታጣቂው ቡድን አመራሮች በኮንፈረሱ ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ አንፃራዊ ሠላም መምጣትና የዜጎች ሞትና መፈናቀል ለማስቀረት እንዲሁም ለእርቀ ሰላም መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ምስጋና በማበርከት እርቀ ሠላሙ መካሄዱን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.