የሀገር ውስጥ ዜና

የምርጫ ውጤትን ጨምሮ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልሎች መድረሳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርጫ ውጤትን ጨምሮ የምርጫ ቁሳቁስ ከሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ወደ 13ቱ የምርጫ ክልሎች መድረሳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ አስታወቀ፡፡

የማስተባበሪያው ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ አክሊሉ ለጣቢያችን እንዳሉት፥ ከ1 ሺህ 128ቱ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ውጤትን ጨምሮ ሁሉም የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልሎች ደርሰዋል፡፡

ውጤት የመደመር ስራውም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱ በክልል ደረጃ ተደምሮ ዛሬ ይፋ እንደሚሆንም ነው የተናገሩት አስተባባሪው፡፡

የምርጫ ግብዓቶቹ ችግር ሳይደርስባቸው ወደየ ምርጫ ክልሎች እንዲደርሱ ጠንካራ ጥበቃ ያደረገውን የጸጥታ አካልም አመስግነዋል፡፡

በቀጣይም ከምርጫ ክልሎች ወደ ዞን በመሰብሰብ ለምርጫ ቦርድ ተመላሽ የሚሆን ቁሳቁስ እንዲመለሱ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

ህብረተሰቡም ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው መገናኛ ብዙሃን እውነታውን ለህዝብ ለማድረስ የነበራቸውን ትጋትም አድንቀዋል፡፡

በሳምራዊት የስጋት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!