የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በነገው እለት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ክፍት እንደሚሆኑ አስታወቁ

By Tibebu Kebede

June 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው እለት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ክፍት እንደሚሆኑ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት ለ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሰኞ በተዘጉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምትክ ነገ የሥራ ቀን እንደሚሆን መገለጹን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ስለሆነም ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በነገው እለት ክፍት ሆነው አገልግሎት ይሰጣሉ ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!