Fana: At a Speed of Life!

በካናዳ በበጀት ዓመቱ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ376 ሺህ ዶላር ባላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ በካናዳ በተለያዩ ግዛቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ376 ሺህ ዶላር ባላይ ገቢ መሰብሰቡን በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በካናዳ የተቋቋመው የጥምረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የማኒቶባ ቻፕተር በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባባበር የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በካናዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ÷ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እያደረጉ የሚገኙት ተከታታይ የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም ለታላቁ የህድሴ ግብ ከ376 ሺህ ዶላር ባላይ ገቢ መሰብሰቡን መቻሉን ነው አማባሳደሯ የተናገሩት፡፡

በተደረገው የበይነ መረብ ውይይትም 44 ሺህ 575 የካናዳ ዶላር ነጻ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ÷ 13 ሺህ 550 ዶላር ደግሞ ነጻ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መገባቱን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም 47 ሺህ 900 የካናዳ ዶላር የቦንድ ግዢ በቀጥታ ከሀገር ቤት ለመፈጸም ቃል መገባቱንም ነው የገለጹት አምባሳደር ናሲሴ፡፡

ኢትዮጵያውያኑም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ሙሌት እንዲሳካ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ የራሷን ተፈጥሮ ሃብት ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት ለማላቀቅ የምታደርገውን ጥረት ለማሰናከል ከውስጥና ከውጭ የተጋረጠባትን ጫና ለመቋቋምም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.