Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የክረምት የበጎ ፈቃድ አግልግሎት ማስጀመሪያ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት በበጋ በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር ከ870 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገልጿል፡፡

በጎ ፍቃደኝነት ለመደጋገፍና መግባባት በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብርን በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡

በማስጀመሪ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም በሙያቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን ሲሰጡ የቆዩ የህክምና ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ የስነ ህንጻ እና ምህንድስና ባለሙያዎች፣ መምህራን እንዲሁም የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የዘንድሮው ከተማ አቀፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የ43 የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የተጀመረ ሲሆን ÷ 100 ህጻናትን በጉዲፈቻ ለመውሰድ መታቀዱም ተነግሯል::

ከዚህ ባለፈም በርካታ ቤተሰቦችን የቤተሰብ ትስስር በማድረግ ዘላቂነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱ ነው የተገለጸው፡፡

በሃይማኖት እያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.