Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ጎንደር ዞንና የጎንደር ከተማ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በምርጫው አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞንና የጎንደር ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ምክክር አካሂደዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ስምንት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው የተሳተፉት፡፡
ከውይይቱ በኋላ ፓርቲዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ ÷ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅድመ ምርጫ በሀገራዊ ጥቅሞች ላይ ያተኮሩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፓርቲዎች በየሳምንቱ በመገናኘት የምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦትና የምርጫ ቁሳቁስ በተሳካ ሁኔታ ማሰራጨት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሲመክሩ እንደነበርም ተመላክቷል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ በምርጫ ወቅት የምርጫ ቁሳቁስ መሟላቱን እንዲሁም ታዛቢዎች በጣቢያዎች መገኘታቸውን እንዳረጋገጠ በመግለጫው አመላክቷል፡፡
በመድረኩ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጎላ ጥረት ማድረጋቸውም ተገምግሟል፡፡
ከምርጫ ውጤቱ በኋላ ፓርቲዎች ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን እና በቀጣይ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት መወሰናቸውንም አረጋግጠዋል።
በስንታየሁ አራጌ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.