Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “አረንጓዴ አሻራዬን አሳርፋለሁ፤ የኢትዮጵያን ብልፅግና አረጋግጣለሁ!” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፉ የሴቶች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባንጃ ወረዳ ተካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩ በብልጽግና ሴቶች ሊግ አስተባባሪነት የተካሄደ ሲሆን ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሴቶችን ያካተተ ነው፡፡
በመረሃ ግብሩ የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበራት ዘርፍ ሚንስትር ዶክተር አለሙ ስሜን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ፣ ሌሎች የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሃላፊ የትዋለ ጌታነህ በክረምቱ ወራት በብሔረሰብ አስተዳደሩ 105 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ መናገራቸውን ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.