አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት የበርበራ ወደብ ኮሪደር ምርቃት ላይ የተሳተፋ የሶማሌ ክልል ልዑካን በሀርጌሳ ከተማ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በዚህም አቶ ሙስጠፌ እና ሌሎች የሶማሌ ክልል አመራሮች በሶማሌ ላንድ ቤተመንግሥት ከሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂና ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በህዝብ ለህዝብ ትስስር፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በቀጠናው ሰላም ዙሪያ መምከራቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!