Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ስራ ከጀመረ አንስቶ ከ550 በላይ ጊዜ በአሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶበታል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ስራ ከጀመረ ጀምሮ ከ550 በላይ ጊዜ የመኪና አሽከርካሪዎች በንብረት ላይ ጉዳት እንዳደረሱበት አስታውቋል ።
ዛሬ ዑራኤል አካባቢ ቪትዝ ተሽከርካሪ የባቡሩን አጥር ሰብሮ መግባቱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ለፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።
ይህን ተከትሎም ለሶስት ሰዓት ያህል የባቡር ትራንስፖርት አግልግሎት መቋረጡን ነው የገለጹት።
ያደረሰው ጉዳትም ከሁለት ቀን በኃላ ግምቱ እንደሚታውቅ ጠቅሰው የባቡር ትራንስፖርት አግልግሎቱ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡
በተደጋጋሚ ከጦር ሀይሎች እስከ አያት በሚደርሰው የባቡር መስመር ላይ የመኪና አሽከርካሪዎች የባቡሩን አጥር ሰብረው በመግባት የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ነገር ግን እስካሁን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ነው ያሉት፡፡
የመኪና አሽከርካሪዎች በቀንም ሆነ በሌሊት ሲያሽከርክሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ፎቶ-ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.