Fana: At a Speed of Life!

ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውሉ 20 ሺህ የቀርከሃ አልጋዎች አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውሉ 20 ሺህ የቀርከሃ አልጋዎችን ለጤና ሚስኒስቴር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቀርከሃ አልጋዎቹ ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት( ጂ አይ ዜድ) በተገኘ ድጋፍ የተሰሩ መሆኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ኮሮና ቫይረስን በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ጂ አይ ዜድ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር በበኩላቸው ÷ የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሃረላ አቡዱላሂም ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ላከናወነው ተግባር ምስጋና እና እውቅና ሰጥተዋል፡፡

ድጋፉ የኮቪድ -19 ህሙማን ወደ ህክምና ሲገቡ ሊከሰት የሚችለውን የአልጋ እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.