Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቢያትሪስ ዋኒ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው አምባሳደር ነቢል በኢትዮጵያ የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያሸነፉበት ነጻና ሰላማዊ ምርጫ ሆኖ መጠናቀቁን ለሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በጎረቤት አገራት ለማስፋት የተያዘውን ዕቅድ ለሚኒስትሯ ገልፃ አድርገዋል።
በዚሁ መሠረት የችግኝ ተከላው የፊታችን ሐምሌ 2 ቀን 2013 የሚከበረው የደቡብ ሱዳን 10ኛ ዓመት የነጻነት ክብረ-በዓል አንድ አካል እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን ጠቁመዋል።
ሚኒስትሯም ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ችግኝ መትከል ለአካባቢ ጥበቃና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ ለመርሐ-ግብሩ ተግባራዊነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.