Fana: At a Speed of Life!

”አዲስ አበባን እናልብሳት “በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ተካሄደ 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  “ኑ አዲስ አበባን እናልብሳት “በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ  ከተማ ደረጃ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በጉለሌ እጽዋት ማዕከል ተካሄደ ።

በመርሐግብሩምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ÷  አዲስ አበባ እናልብሳት ብለን በምርጫው እለት በአንድ እጅ ዴሞክራሲን በሌላ እጅ ደግሞ ችግኝ መትከል ጀምረናል ብለዋል።

በዘንድሮ የክረምት ወራት የችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል በእቅድ መያዙን  ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም ነዋሪዎች፣የፌደራል እና የሴክተር ተቋማት ከተማዋ ለኑሮ ምቹ እንድትሆን በየአካባቢው ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋል።

የፌደራል እና የሴክተር ተቋማት ፣ለኤምባሲዎች እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንዲህም ሌሎች አካላት የችግኝ መትከያ ስፍራዎች መዘጋጀቱን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

ህብረተሰቡም ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ÷ ለነገው ትውልድ አረንጓዴን ለማልበስ ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሐግብሩ በእንግድነት ተገኝተው ችግኝ የተከሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የትብብር እና የአንድነት እንቅስቃሴ ለክልሎች ምሳሌ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በዘንድሮ የክረምት ወራት የችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7ነጥብ5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል በእቅድ የተያዘ ሲሆን በሰኔ 14 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ጎን ለጎን 2 ነጥብ 58 ሚሊየን ችግኞች መትከል መቻሉም ተገልጿል።

በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ  ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ሚኒስትሮች ፣ ፣አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የስፖርት ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.