Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ጊዜ የታየው መደማመጥ እና በሀሳብ የበላይነት ብቻ ማመን  አሁንም በልማቱ እንዲቀጥል የጋሞ ዞን ፖለቲካ ፖርቲዎች ጠየቁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የጋሞ ዞን ፖለቲካ ፖርቲዎች የ6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።

የጋሞ ዞን ፖለቲካ  ፖርቲዎች  የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ  ወንድሙ ኡቶ÷ በምርጫ ጊዜ የታየው መደማመጥ እና በሀሳብ የበላይነት ብቻ ማመን  አሁንም በልማት እና በሌሎች ሥራዎች ላይ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል አሳሰበዋል።

ከድህረ  ምርጫ በኃላ ከመለያየት ይልቅ አንድ በሚያደርጉና በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በጋሞ ዞን 10 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች  መወዳደራቸዉን ያመላከቱት ኃላፊዉ÷  በዞኑ ባሉት 10 የምርጫ ክልሎች ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ ለመስራት የታቀዱ ዕቅዶች የተሳኩ ነበረም ብለዋል ።

አሁን ሀገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የምርጫ  ምህዳርን ለማስፋት ላደረጉት ድጋፍ በፖርቲዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል ።

በጋራ ምክር  ቤቱ ስብሰባ ላይ የተገኙት የፖርቲ አባላት ፣በምርጫ ሂደት ላይ የታየው አንድነት እና በሃሳብ የበላይ የማመን ልምድ እንዲጠናከር ጠይቀዋል ።

የፖርቲዎች  አባላት ቀጣይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዩች ላይ በመግባባት ፣ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ለመስራት መክረዋል ።

በማቴዎስ  ፈለቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.