Fana: At a Speed of Life!

የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ተመስርቷል።

በትግራይ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግርና ከመጠለያ ጣቢያው አመሰራረት ክፍተት ምክንያት የተዘጉት የሽመልባና ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ተመሰረቱ።

የኤርትራ ስደተኞችን የሚያስተናግደው መጠለያ ጣቢያ የምስረታ ስነ-ስርዓት በዳባት ወረዳ ተካሂዷል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ÷ ኢትዮጵያ ስደተኛን የማስተናገድ ረዘም ያለ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን ገልፀው÷ የአካባቢው ማህበረሰብ የስደተኞችን ደህንነት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ተወካይ አን ኢንኮንትሬ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ስደተኛን በማስተናገድ ሁነኛ አጋራችን ናት በቀጣይ በትብብር መስራታችን እንቀጥላለን ብለዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያለ አለም ፈንታሁን÷ የአካባቢው ማህበረሰብ ስደተኞችን ተቀብሎ የማስተናገድ ባህሉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በሽመልባና ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች በአዲሱ መጠለያ ጣቢያ የሚጠለሉ ሲሆን ÷ መጠለያ ጣብያዎቹ ከ15 እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞችን ያስተናግዳሉ ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.