ዓለምአቀፋዊ ዜና

የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ 22 ዓመት ከ6 ወር የእስር ቅጣት ተወሰነበት

By Tibebu Kebede

June 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ-አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ዴሬክ ሾቪን 22 አመት ከ6 ወራት የእስር ቅጣት ተወሰነበት፡፡

የቀድሞው ፖሊስ ባልደረባ የሆነው ሾቪን ጆርጅ ፍሎይድን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ ይታወሳል፡፡

ባለፈው የፈረንጆቹ አመት የተፈጸመው ግድያ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከተለቀቀ በኋላ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሶ ነበር፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦችን ጨምሮ በርካቶች የቀድሞው የፖሊስ ባልደረባ በፈጸመው ወንጀል እንዲቀጣ ሲጠይቁም ነበር፡፡

ሁኔታው ከአመት በኋላ የፍርድ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን አሰቃቂ ግድያው የፈፀመው የቀድሞው የፖሊስ መኮንን በተመሰረተበት ክስ በ22 ዓመት ከ6 ወር በእስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ሾቪን በ30 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ቢጠይቅም ውሳኔው በ22 አመት ከ6 ወር መጽናቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች ውሳኔው መልካም ቢሆንም ለወንጀሉ የቅጣት ጣሪያው እንዲወሰንበት ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!