ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የቁልምሳ ምርምር ማዕከል 71 ሔክታር መሬት ማልማት የሚያስችል የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክት አስገንብቶ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ በ ኤ ጂ ፒ አማካኝነት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ሲሆን ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበትም ተነግሯል።
በማዕከሉ የተገነባው ይህ ፕሮጀክት በአመት ሁለት ጊዜ የምርምርና የዘር ብዜትን ለማከናወን እንደሚያስችል የምርምር ማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ቶሎሳ አለሙ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ የምርምርና የመነሻ ዘር ብዜትን በአመት ሁለት ጊዜ ለማከናወን ከማስቻሉም ባሻገር የክረምት ወራትን ብቻ ጠብቆ ይሰራ የነበረውን ጎታች አሰራር እንደሚያስቀር የማዕከሉ ዳይሬክተር ጠቁመዋል።
ይህ ደግሞ ማዕከሉን በበጋም የምርምር ተግባራትን እንዲያካሔድ ያስችለዋል ሲሉም ገልፀዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እደገለፁት ማዕከሉ አዳዲስ የግብርና ምርምር ውጤቶችን በማከናወን በግንባር ቀደም እንደሚጠቀስ ገልፀው ይህ ደግሞ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገው ነው ብለዋል።
በጋሻው አርጋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!