የሀገር ውስጥ ዜና

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ፖሊሲ የህግ ማዕቀፎች ማረጋገጫ አውደ ጥናት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

June 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ፖሊሲ የህግ ማዕቀፎች ማረጋገጫ አውደጥናት በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ።

ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት፣ መንግስትና ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር የህግ ማዕቀፍ ግብአት የሚሆኑ ምክረ ሃሳቦችም ተነስተውበታል።

የኢትዮጵያን ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ባለቤት የሆኑ አካላት በጋራ አለመስራታቸው ዋናው ችግር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ አንጻርም ችግሮቹን ለመፍታት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ትስስር መፈጠሩ ብቁ ለውድድር የሚቀርብና በተግባር አቅሙን ያጎለበተ የሠው ሀይል ለማፍራትና የስራ አጥነት ችግርም ለመቅረፍ ይረዳል ተብሏል።

በሰላማዊት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!