Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያን እናልብስ” የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል 3ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ፡፡

የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ 3 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብርን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ ከፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በይፋ አስጀምረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ቀን በከተማም ሆነ በገጠር ያማከለ ስራ የሚሰራ ሲሆን በሀገሪቱ የአየር ሁኔታ ተፅዕኖዎችን መቋቋም እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የሚያስችል መሆኑን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም ማርሻሎ ተናግረዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም ማርሻሎ፣ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎችና የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.