የሀገር ውስጥ ዜና

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ

By Tibebu Kebede

June 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ኬንያውያን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ቀጠናውን ለማስተሳሰር እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

1 ሚሊየን ችግኞችን በዘንድሮው ክረምት በኬንያ የሚተከል ሲሆን እንዲህ አይነት መርሃ ግብሮች የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲ በማጠናከሩ ረገድ ሚናው ትልቅ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ኬንያ ዛፍ የመንከባከብ እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ማህበረሰቡ ላይ የሰራችው ስራን ኢትዮጵያ ልትጋራው የሚገባ መሆኑ ተነግሯል።

በብስራት መለሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!