Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ምክር ቤት ከ630 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት ባካሄደው ሶስተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ከ630 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ጉባኤ ተጨማሪ በጀቱን ያፀደቀው የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ሀሰን አማካኝነት በቀረበው የበጀት ረቂቅ ላይ ከተወያየ በኋላ ነው።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ለመደበኛ በጀትና በክልሉ ለተከናወኑ ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ወጪ 630 ሚሊየን 241 ሺህ 375 ብር ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የበጀቱም ምንጭ ከክልሉና ከተማ አስተዳደሮች የውስጥ ገቢዎች የሚሸፈን መሆኑን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮው ሃላፊው ገልጸዋል።

ጉባኤው ነገም ቀጥሎ ሲውል በክልሉ ዋና ዋና የአስፈጻሚ አካላት 11 ወራት ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ የሶስት አስፈጻሚ አካላትን ተግባርና ሃላፊነት ለመደንገግ የወጡ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.