የሀገር ውስጥ ዜና

ለምርጫው ስኬታማነት ጉልህ ድርሻ ያበረከቱ አካላት የሀገር ባለውለታዎች ናቸው – አቶ እርስቱ ይርዳው

By Tibebu Kebede

June 27, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማነት ጉልህ ድርሻ ያበረከቱ አካላት የሀገር ባለዉለታዎች ናቸው አሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው።

ክልሉ በቀጣይ የድህረ ምርጫ የልማት ተግባራትን እንዴት ያሳካ በሚል ውጥን ላይ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ መክረዋል።

በበልጉ የዝናብ እጥረት የተከሰተውን የምርት ቅናሽ፣በመኸሩ ማካካስ የሚያስችል እቅድ ቀርቦ የተወያዩ ሲሆን የኢትዮጵያን እናልብስ ዘመቻ አካል የሆነውን የአርንጓዴ ልማት አሻራን የማኖር ስራዉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሰፉፊ ስራዎች እንደሚሰሩም በደሬቴ የገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!