Fana: At a Speed of Life!

የሚንስቴር መ/ቤቱ ሰራተኞች ከ4ሺህ በላይ ችግኞችን ተከሉ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ሰራተኞች በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሚ ወረዳ “በኢትዮጵያን እናልብስ” አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ነው ችግኞችን የተከሉት።

የትራንስፖር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ ለትውልዱ አረንጓዴና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ችግኝ ከመትከል ባለፈ በቀጣይ ጊዜያት ከአከባቢው ማህበረስብ ጋር በመቀናጀት ተንከባክቦ ማሳደግ እንደሚገበ አሳስበዋል።

በተለይም የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሞተር አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጂ በመንደፍ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኗን ጠቅሰዉ ፣ ከትራንስፖርት ዘርፍ የሚወጡ በካይ ጋዞችን በመቀነስ የአየር ብክለትን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል።

በዓመቱ ተቋሙበአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራሙ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ተናግረዋል።

ምንጭ:- አሚኔ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.