የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች መፍትሄ ይፈልጋሉ-የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር

By Tibebu Kebede

June 27, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በሰላም ሚኒስቴር በኩል መፍትሄ እንዲገኝ መግባባት ላይ መደረሱን የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር አስታወቀ።

ከክልሎች ጋር በነበረ ውይይት ላይ የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባውን ተሳትፈዋል።

በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በተመለከተ በሰላም ሚኒስቴር በኩል መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን መግባባት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ።

በቀጣይ አመትም ከዘርፉ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል።

እቅዳችን እንዲሳካም በዘርፉ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ማስተካከል ከኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

ኢትዮጵያ ከማአድን ሀብቷ እያገኘች ያለችው ገቢ በከፍተኛ መጠን ጭማሪ እያሳየ ይገኛል ነው ያሉት ኢንጅነር ታከለ።

በተያዘው አመትም ከፍተኛውን ገቢ ከማአድን ዘርፍ አግኝተናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!