Fana: At a Speed of Life!

ሌ/ጀኔራል አስራት ዴኔሮ በመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ያለው ስራ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተመራ ቡድን በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝቷል።

ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በዞኑና በወረዳው አማካኝነት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ተናግረዋል።

በዞኑ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ በበኩላቸው ÷ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከዞን እስከ ወረዳ የተዋቀረ የባለሙያ ቴክኒካል ቡድን በማሰማራት ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ተፈናቀለው የነበሩና አሁን በነበሩበት ቦታ በመቋቋም ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም ከዕለት ምግብ አቅርቦት በተጨማሪ እንደ ወፍጮ ቤትና የጤና ተቋማት እንዲሟሉላቸው መጠየቃቸውን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.