የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የሚገነበው የአማራ ባህል ማዕከል አልማ ለሚያከናውነው የልማት ስራ አጋዥ እንደሚሆን ተገለጸ

By Tibebu Kebede

June 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባህል ማዕከል ግንባታ የአማራ ህዝብ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ እንዲቆይ ከማድረግ ባሻገር የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ የአማራ ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ርክክብን በማስመልከት የምስጋና መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የባህል ማዕከሉ አልማ የሚያደርጋቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚደግፍ መሆኑን የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ÷ አልማን መደገፍ በአማራ ክልል በድህነት ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎችን መደገፍ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በመድረኩ የተሳተፉት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ÷ የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር ሆኖ ሀገሪቱን ለመገንባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የባህል ማዕከሉ ግንባታ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለግንባታው ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡