በትምህርት ዘርፍ የሰኔ 30 አረንጓዴ አሻራ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብስ”መርሃ-ግብር ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ ይጀመራል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፍ የሰኔ 30 አረንጓዴ አሻራ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብስ” ሀገራዊ መርሃ-ግብር ነገ በአርባምንጭ ከተማ ይጀመራል።
በመረሃ-ግብሩ ለመሳተፍ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣የ12 ክልሎች የትምህርት ቢሮ እና የመምህራን ማህበር ኃላፊዎች እና ሰራተኞች አርባምንጭ ከተማ ተገኝተዋል።
በዛሬው ዕለትም በአርባምንጭ ከተማ ከሚገኙ የቱሪስት መስህቦች መካከል የአርባምንጭ ተፈጥሮ ደን ፣ የአዞ ራንች አርባ ምንጮች እና የአባያ ሀይቅን ጎብኝተዋል።
የትምህርት ዘርፍ “ሰኔ 30 አረንጓዴ አሻራ “ችግኝ ተከላ ሀገር አቀፍ መርሃ-ግብር ነገ በአርባምንጭ ከተማ የሚጀመር መሆኑን ከጋሞ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡