ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ በኢራን በሚደገፉ የኢራቅ እና ሶሪያ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ፈጸመች

By Tibebu Kebede

June 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢራን በሚደገፉ የኢራቅ እና የሶሪያ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል፡፡

የአየር ላይ ጥቃቱ ታጣቂ ቡድኖች ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ለፈጸሙት የድሮን ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በትናንትናው ዕለት በተፈጸመው በዚህ ጥቃትም በአማጺ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዝን ላይ ጉዳት ማድረስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በጥቃቱ አምስት የሚደርሱ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን ÷ በርካቶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጀ ባይድን በተለያዩ ሀገራት ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ አሜሪካ ወታደሮችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊው አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የአሜሪካ ጦር በኢራቅ እና ሶሪያ ድንበር አካባቢ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ ሲወስድ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡

ምንጭ ÷ አልጂዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!