Fana: At a Speed of Life!

ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ  12 እስከ 18 ቀን 2013  ዓ.ም ድረስ ከ 56 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከኮንትሮባንድ እቃዎቹ መካከል ግምታዊ ዋጋው ከ33 ሚሊየን 100 ሺህ ብር  የሆነ ለዕርዳታ እንዲውል ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ አገር ገብቶ በጅግጅጋ ሲንቀሳቀስ የተያዘ ስንዴ ይገኝበታል፡፡

በሳምንቱ የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 54 ሚሊየን 211ሺህ 562 ብር እንዲሁም ወጪ  2 ሚሊየን 722ሺህ 916  ብር ግምት እንዳላቸው ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ከእቃዎቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ ስንዴ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ እቃዎች ፣ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን 32 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ ተይዘዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.